Song Lyrics

ደስ ይበለን

Roman Samuel
Negeru Tegelebete
እያንዳንዱ ቀን ክፉ ነው መልካም መዓዛ ጣዕምም የለው የትም ብንሄድ ምንም ብንይዝ ሁሉም ነገር አለው መዘዝ ነገር ግን ዓይኖቻችንን ወደ ጌታ ስናቀና የሚያስደስተን ብዙ ነው የሚሞላን በምሥጋና እስቲ የላዩን እናስብ የምድሩን እንተወውና ደስ ይበለን (4x) ሃሴት እናርግ ዕልል እንበል በምድር ጥበብ ጥበበኞች ሃያላን ባላባቶች ብርቱዎችም ደግሞ እያሉ የሰውን ምስፈርት የሚያሟሉ ሥጋን የለበሰ ሁሉ እንዳይመካ በከንቱ የዓለምን ሞኝ ምናምንቴ ደካማዎችን መምረጡ የሚያስፈነድቅ ተዓምር ነው እንደ እኛ ዓይነቱን መጥራቱ ደስ ይበለን (4x) ሃሴት እናርግ ዕልል እንበል በልዩ ልዩ ፈተና ሃዘን ዛሬ ቢጐበኘንም እምነታችን እንዲነጥር ፈትና ቢደርስብንም ከተዘጋጀልንና ሊገለጥልን ካለው ክብር ልንወርሰው ከምንጥብቀው ከማይጠፋው ርስታችን ጋር ሲመዛዘን ሥፍራም የለው ከቶም አይገባም ከቁጥር እግዚአብሔር አምላክ ነው ደስ ይበለን እኛም ደግሞ ሕዝቡ ደስ ይበለን በክርስቶስ ዋጅቶን ደስ ይበለን አርጐናል ገንዘቡ ደስ ይበለን ከሞት መንጋጋ ውስጥ ደስ ይበለን ነጥቆ አውጥቶናል ደስ ይበለን በክንዱ መድሃኒት ደስ ይበለን ሕያዋን አርጐናል ደስ ይበለን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection