የከበበኝ የደገፈኝ አሃሃ የቀደመኝ የተከተለኝ (2x) አምላኬ ነው የሚያኖረኝ (6x) እግዚአብሔር ነው የጓደኛዬ ነገር የአየሩ ሁኔታ የዘመን ወጣ ውረድ የጠላት ድንፋታ አይደለም ሚዛኔ ነገን የምለካበት ቃልኪዳን ይዣለው እምነቴን የምጥልበት እርሱ አይለወጥም አምላኬ አይለወጥም እግዚአብሔር አይለወጥም ስለዚህ እኔ አልጠፋም (3x) የከበበኝ የደገፈኝ አሃሃ የቀደመኝ የተከተለኝ (2x) አምላኬ ነው የሚያኖረኝ (6x) እግዚአብሔር ነው የጨባጭ መረጃ ቢያቀብለኝ ኖሮዬ እኔም መረጃ አለኝ ቃል ሰጥቶኛል ጌታዬ እስከ ዛሬ ድረስ አቤነዘር ብያለሁ ትናንት የረዳኝን ነገም እታመነዋለሁ እርሱ አይለወጥም አምላኬ አይለወጥም እግዚአብሔር አይለወጥም ስለዚህ እኔ አልጠፋም (3x) የክብር አምላክ የክብር አብሮኝ ሆነና እግዚአብሔር ያስጨነቀኝ አዋረዳቸው እንደ መንገድ ጭቃ ረገጣቸው የክበር ንጉሥ የክብር ቀድሞኝ ወጣና እግዚአብሔር ጠላቶቼን ሁሉ አወካቸው እንደ ትብያ እንደ እብቅ በተናቸው እርሱ አይለወጥም አምላኬ አይለወጥም እግዚአብሔር አይለወጥም ስለዚህ እኔ አልጠፋም (3x) መብልና መጠጥ የድንኳኔ ውበት መቀበሪያ ሥፍራ የአሟሟቴም ዓይነት አይደለም ጭንቀቴ እኔን የሚያሳስበኝ ከዚህ የሚሻገር የደመቀ ተስፋ አለኝ እርሱ አይለወጥም አምላኬ አይለወጥም እግዚአብሔር አይለወጥም ስለዚህ እኔ አልጠፋም (3x) የከበበኝ የደገፈኝ አሃሃ የቀደመኝ የተከተለኝ (2x) አምላኬ ነው የሚያኖረኝ (6x) እግዚአብሔር ነው