እግዚአብሔር ቸር (3x) ምህረቱ ለዘለዓለም እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና ወደ ደጆቹ በመገዛት ኑና ወደ አደባባዮቹም ግቡ በምሥጋና ኑና ግቡ በምሥጋና ፀጋው ያዳናችሁ አመስግኑት ፍቅሩ የገባችሁ አመስግኑት ምህረቱን ተነጋገሩ ፀጋውን ተነጋገሩ ፍቅሩን ተነጋገሩ በማስተዋል ለእርሱ ዘምሩ ከሞት የወጣችሁ አመስግኑት ምህረቱን ያያችሁ አመስግኑት ተዓምራቱን ተነጋገሩ ጽድቁን ተነጋገሩ እውነቱን ተነጋገሩ በማስተዋል ለእርሱ ዘምሩ አባት የሆናችሁ አመስግኑት ጉያው ያሞቃችሁ አመስግኑት ቸርነቱን ተነጋገሩ ደግነቱን ተነጋገሩ አባትነቱን ተነጋገሩ በማስተዋል ለእርሱ ዘምሩ ሃሌሉያ (4x) በሉ