Song Lyrics

ዛሬም ይኸውልህ

Roman Samuel
Negeru Tegelebete
በዘመናት ግን አላረጀህም የዓመታት እርዝማኔ አላታከተህም ትናንት ዛሬ ለዘለዓለም አንተ ያው አንተ ነህ ኃያል ንጉሥ እግዚአብሔር የምትገርም አምላክ ነህ (5x) እንኳን አመለኩህ አንኳን ሰገድኩልህ ገናም አልበቃኝም ዛሬም ይኸውልህ አዲስ ምሥጋና (4x) ዛሬም ይኸውልህ (5x) ማልጄ ልዘምር ደግሞም ቀን በቀትር ምሽትም ጨምራለሁ ይኼም ሲያንስህ ነው (2x) ምሥጋናዬ አይነስህ ይደራረብ በመቅደስህ (2x) ብዙ አማልክት ወድቀዋል ለጥቂት ተደንቀው(?) መታሰቢያ እንኳን አጥተዋል ዘመን አልፎባቸው አንተ ግን እንዳማረብህ በዙፋንህ ላይ ነህ ኃያል ንጉሥ እግዚአብሔር እጅግ ድንቅ አምላክ ነህ (5x) እንኳን አደነኩህ እንኳን ሰገድኩልህ ገናም አልበቃኝም ዛሬም ይኸውልህ አዲስ ምሥጋና (5x) ዛሬም ይኸውልህ (5x) በታላላቅ ጉባኤ በጓዳም ለብቻዬ መስዋዕቴ ያርግልህ ጣፋጭ መዓዛ ይሁንልህ (2x) አምልኮዬ አደነልህ ይደራረብ በመቅደስህ (2x) ፍቅር ምህረት ቸርነትህ ማልዶ ማልዶ አዲስ ነው አሮጌ ታሪክ የለህም ብርታትህም ያው ነው የቅድስናህም ክብር እያደር ይደምቃል ኃያል ንጉሥ እግዚአብሔር ዝናህ ምድርን ሞልቷል (5x) እንኳን አወደስኩህ እንኳን ዘመርኩልህ ገናም አልበቃኝም ዛሬም ይኸውልህ አዲስ ምሥጋና (5x) ዛሬም ይኸውልህ (4x) ካየሁት ከሰማሁት ለነፍሴ የቀረላት በአንተ መደነቅ ነው ዋናም ትርፍም የሆነላት (2x) ምሥጋናዬ አይነስህ ዝማሬ አይነስህ አምልኮዬ አይነስህ አክብሮት አይነስህ ይደራረብ በመቅደስህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection