ምህረቱ እንደ ደመና (2x) ከቦኛል ልዘምር የአምላኬን ምሥጋና (2x) የዘወትር ትዝታው ማስታወሻው እኔን ባየኝ ቁጥር ትዝ የሚለው የሕይወት እስትንፋስ የሆነልኝ ከምህረቱ በቀር ምንም የለኝ ጽድቄ ቅድስናዬ ቤዛነቴም ኢየሱስ ነው የመዳን ልብሴ መጐናጸፊያዬም እርሱ ነው ትልቅ ልግስናው ቸርነቱ ብቃት ሆኖ ያቆመኝ በፊቱ የማንነቴ ምንጭ መገኛዬ ይቅርታው እኮ ነው የጌታዬ ነፍሱን ሰጥቶ ነፍሴን የተቤዛት ኢየሱስ ነው በደሙ አጥቦ አዲስ ንፁህ ያደረጋት እርሱ ነው የረከሰ ማንነቴን ሽሮ አደፋውን ታሪኬን ቀይሮ በወይኑ ግንድ ላይ የተከለኝ በአደባባዮቹም ያበቀለኝ አክሊል እንደለበሰ ሙሽራ ያስዋበኝ ኢየሱስ ነው ሞገስ ደም ግባት ዝርግፍ ጌጥ የሆነኝ እርሱ ነው በምህረቱ ልጁ ሆኛለሁ በምህረቱ ቤቱ ኖራለሁ በምህረቱ አመልከዋለሁ በምህረቱ አገለግላለሁ ምህረቱ ሕይወቴ ምህረቱ ጉልበቴ ምህረቱ ብቃቴ ምህረቱ ትምክህቴ ምህረቱ እረፍቴ ምህረቱ ምችቴ ምህረቱ ተድላዬ ምህረቱ ጥላዬ