Song Lyrics

ነገሩ ተገለበጠ

Roman Samuel
Negeru Tegelebete
ተሳዳጅ እፎይ ሲል አሳዳጅ ሬሳበሬሳ እግዚአብሔር ክንዱን ሲያነሳ ጭንቅ ውስጥ አገባቸው አሳያቸው ፍዳ አበሳ አንሸሽም ቢሉ የማይሆን ሆነ ነገሩ ሠራዊቱ ታወከ መንከራኩሮቹ ታሰሩ ባሕሩ ከደናቸው ደግሞ ሳይተያዩ እስራኤል ተሻገረ ለዘለዓለም ተለያዩ[1] አዝ፦ ነገሩ ተገለበጠ እግዚአብሔር ሕዝቡን አስመለጠ ነገሩ ተገለበጠ አዋጅ በአዋጅ ተሻረ ሞት በሕይወት ተቀየረ እግዚአብሔር ተነሳ ንጉሡን እንቅልፍ ነሳው የተዘጋን መዝገብ እንዲያገላብጥ አደረገው መታሰብ ሆነና ሃዘን በደስታ ተተካ ሁኔታው ሲለወጥ ሰቃይ ተሰቃይ ነው ለካ ዋይታና ስቃይ ጭንቀት ሃፍረት ለጠላታቸው በአይሁድ የተድላና የደስታ ቀን ሆነላቸው[2] አዝ፦ ነገሩ ተገለበጠ እግዚአብሔር ሕዝቡን አስመለጠ ነገሩ ተገለበጠ አዋጅ በአዋጅ ተሻረ ሞት በሕይወት ተቀየረ ከአምላካቸው በቀር ቅዱሳን ስግደት አያውቁም ሚቆጣ ቢቀጣ ጣዖትን ከቶ አያመልኩም ሰባት እጥፍ ቢነድ እቶኑ ቢብስበትም ያድናል እርሱ አንሰግድም ባያድነንም የጣሏቸው ሰዎች ወሳፈን ገደላቸው የልዑል አምላክ ባሮች ክብር ተጨመረላቸው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection