Song Lyrics

ዘላቂ ዋስትና

Roman Samuel
Negeru Tegelebete
በኃጥያት ባርነት ከታሰርንበት የሞትን ሽታ ካጣጣምንበት ወደ ፅድቅ አደባባይ ጠርተኸን በሕይወት መዓዛ ይኸው ታወድን የጥሪህ ተስፋ አስደናቂ ነው የርስትህም ክብር እኩያ የለው ስለሰጠኸን የመዳን ዕውቀት ተመካን በኃይልህ ታላቅነት አማኑኤል (6x) አሜን ይብዛልህ ምሥጋና (3x) አስተማማኝ ነህ ዘላቂ ዋስትና ከድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ወጥተና ከሞት ጥላም ሃገር አምልጠናል በሚደነቅ ብርሃን ልታኖረን አዲስ ምዕራፍ ተከፈተልን በቃል ኪዳንህ እየደገፍከን በሸለቆ ህግህን አስተማርከን እስከ ዘንድሮ በአንተ ዘልቀናል ከእጆችህ መዳፍ ማን ያወጣናል አማኑኤል (6x) አሜን ይብዛልህ ምሥጋና (3x) አስተማማኝ ነህ ዘላቂ ዋስትና ማግኘት ማጣት መብዛት መጉደልን መክበር መዋረድ መራብ መጥገብን መነቀፍ መሞገሥም አይተናል ጉልበት ሆነኸን ሁሉን ችለናል ከእኛ ጋራ ነህ ማን ይከሰናል አፀደከን ማን ይኮንነናል ከአሸናፊዎች በአንተ እንበልጣለን የለም ከፍቅርህ የሚነጥለን እንዲህ መተናል ያለፈውን ዘመን ስለ ነገውስ ምን አስጨነቀን ኃያልነትህ እጅግ አስመካን ኦ የእኛ ጌታ ተመሥገንልን ዝማሬ አለን እስከዛሬ ዕልልታ ዘላቂ አለኝታ ጭብጨባ ሽብሸባ የዘለዓለም አምባ እኛስ በጐነት የለንም
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection