ደመና ሆኖብኝ ሁሉ ነገር ጨልሞብኝ ዐይኖቸን አቅንቸ ጌታዬ ሆይ ፍረድልኝ አልኩኝ (ለካ ደመናው ውኃ ያዘለ ነበር ደረቀ ባልኩበት ዝናቡ ወረደበት) (2x) አዝ፦ ነገር ለበጐ ሆኖ አየሁኝ ነገረ ለበጐ (2x) እግዚአብሔር ቅን ፍርድን ፈርዶ ምረቱን ለእኔ አውርዶ እግዚአብሔር ቅን ፍርድን ፈርዶ ምረቱን ለእኔ አግንኖ ፈተናው አዝሎኝ ለመውደቅም ስንገዳገድ ባሕሩን ሲከፍለው በወጀብ ውስጥ አገኘሁኝ መንገድ አምላክ እንደሌለውእንደማንም ለቆጠረኝ የምመስክረው ምናገረው አለኝ (2x) ብቻውን ታምራት ድንቅ ሚያደርግ ነው እኔስ አምላክ አለኝ ሁሉ የተቻለው ብቻውን ታምራት ድንቅ ሚያደርግ ነው እኔስ ጋሻአለኝሁሉ የምተማመነው የምተማመነው ተስፋ የማደርገው ነገሬን በጊዜው ውብ አርጐ ስሪ ነው ያማልክቶቻ አምላክ እምላኬ ኃይለኛ ነው በዘመናት መሃል ጉልበቱ ያልዛለው ቅን ይፈርዳል ለተጠጋው በጊዜው ደርሶ ማባበልን ያውቃል የፈሰሰን እንባን አብሶ የእኔጌታ ለአኔ ምርኮዬን መልሶ እንደገና አቆመኝ ጉልበቴን አድሶ የእኔ ጌታ ለእኔምርኮዬን መልሶ እንደገና አቆመኝ ሕይወቴን አድሶ አዝ፦ ነገር ለበጐ ሆኖ አየሁኝ ነገረ ለበጐ (2x) እግዚአብሔር ቅን ፍርድን ፈርዶ ምረቱን ለእኔ አውርዶ እግዚአብሔር ቅን ፍርድን ፈርዶ ምረቱን ለእኔ አግንኖ