አዝ፦ ውዴ የእኔ ነው እኔም የእርሱ ነኝ (2x) ከሌላው ወዳጄ ይልቅ እጅግ የሚበልጥብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ በእርሱ አትምጡብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ እኔ ወደዋለሁ ምኞቱን አውቃለሁ አላማው ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው (2x) አልተሳሳትኩም እኔ በምርጫዬ ከሞት ሕይወት ይሻላል ብዬ ነፍሴን ሊታደግ በሩን ላንኳኳው ከፈትኩለት ልቤን ኢየሱሴን ላስገባው እርሱም አሜን ሕይወቴን ወረሰው አዝ፦ ውዴ የእኔ ነው እኔም የእርሱ ነኝ (2x) ከሌላው ወዳጄ ይልቅ እጅግ የሚበልጥብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ በእርሱ አትምጡብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ እኔ ወደዋለሁ ምኞቱን አውቃለሁ አላማው ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው (2x) ሞልቶልኝ ከማጣ ኢየሱሴን አልፈልግም መርጣለሁ ሞቴን ፍቅሩን ቀምሼ ወዴት ሄዳለሁ ልለየው አልችልም እጅግ ወደዋለሁ ከእርሱ የተነሳ ከሞት ድኛለሁ አዝ፦ ውዴ የእኔ ነው እኔም የእርሱ ነኝ (2x) ከሌላው ወዳጄ ይልቅ እጅግ የሚበልጥብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ በእርሱ አትምጡብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ እኔ ወደዋለሁ ምኞቱን አውቃለሁ አላማው ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው (2x) አይለወጥም እንደ ሰው አይደለም አምነዋለው ኢየሱስ አይከዳኝም በዘለዓለም ፍቅሩ ስቦኛል ወዶኛል እስከ ሽበት ቢሆን እርሱ ይሸከመኛል ሰልችቶ ውዴ መቼ ይጥለኛል አዝ፦ ውዴ የእኔ ነው እኔም የእርሱ ነኝ (2x) ከሌላው ወዳጄ ይልቅ እጅግ የሚበልጥብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ በእርሱ አትምጡብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ እኔ ወደዋለሁ ምኞቱን አውቃለሁ አላማው ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው (2x) ውርደቴን በክብር ለውጦልኝ የማዳንን ልብስ አለበሰኝ የባርነቴም ቀንበር ሰብሮልኝ ቀና ብዬ እንድሄድ ኢየሱስ አደረገኝ እሰይ ለዘለዓለም ይንገስልኝ አዝ፦ ውዴ የእኔ ነው እኔም የእርሱ ነኝ (2x) ከሌላው ወዳጄ ይልቅ እጅግ የሚበልጥብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ በእርሱ አትምጡብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ እኔ ወደዋለሁ ምኞቱን አውቃለሁ አላማው ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው (2x) ከምንም በላይ አዎ የሚበልጠው ታማኙ ኢየሱስ ባልንፈራዬ ነው ቃሉ ይጣፍጣል ልብን ይደርሳል ውዴ እኮ ልዩ ነው ማንስ ይመስለዋል ምርጫዬ ነው እርሱም እኔን መርጧል አዝ፦ ውዴ የእኔ ነው እኔም የእርሱ ነኝ (2x) ከሌላው ወዳጄ ይልቅ እጅግ የሚበልጥብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ በእርሱ አትምጡብኝ ኢየሱሴን አትንኩብኝ እኔ ወደዋለሁ ምኞቱን አውቃለሁ አላማው ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው አላማውም ፍቅር ነው (2x)