አበርትቶኛል ጉልበቴ እጅግ ዝሎ አሻግሮኛል ዮርዳኖስን ከፍሎ እንዴት እረሳዋለሁ እግዚአብሔርን ከበረት አውጥቶ ከግብጽ ያወጣኝን አዝ፦ ላመስግነው (3x) እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (2x) ልቀኝለት ልቀኝለት ልስገድለት በሕይወት ላቆመኝ ላዳነኝም ከሞት (2x) እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (2x) አስቀድሞ አውቆኛል በሆድ ሳልሰራ መርጦኛል እራሱ ጨለማዬም በራ ዓይኖቼም ማዳኑን እዩ ተዓምራቱን ስለ ፍቅርም ብሎ የሰዋውን ልጁን አዝ፦ ላመስግነው (3x) እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (2x) ልቀኝለት ልቀኝለት ልስገድለት በሕይወት ላቆመኝ ላዳነኝም ከሞት (2x) እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (2x) አስጨናቂዎቼ ሰልፍ አብዝተውብኝ ከአምላኬ ጉያ መስሏቸው የሚነጥቁኝ ግን የማያንቀላፋው ተግቶ የሚጠብቀኝ በዙሪያዬ ካሉት በእውነት አሳረፈኝ አዝ፦ ላመስግነው (3x) እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (2x) ልቀኝለት ልቀኝለት ልስገድለት በሕይወት ላቆመኝ ላዳነኝም ከሞት (2x) እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (2x) እግዚአብሔር ፍቅር ነው በፍቅሩ ይዞኛል እንዳልወድቅም ምርኩዝ ድጋፍ ሆኖልኛል ምን ልበለው እኔስ ውለታው በዛብኝ ሕያዋን ሁላችሁ እስኪ አመስግኑልኝ አዝ፦ ላመስግነው (3x) እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (2x) ልቀኝለት ልቀኝለት ልስገድለት በሕይወት ላቆመኝ ላዳነኝም ከሞት (2x) እግዚአብሔር ለእኔ ባለውለታዬ ነው (2x)