Song Lyrics

ስለተደረገልኝ በጐነት

Roman Lorenso
Geta Bicha Tamagn New
አዝ፦ ስለተደረገልኝ በጐነት ጨምሬ ምለው ምንድን ነው ጨምሬ ምለው ምንድን ነው (2x) ሥራህ ከአእምሮዬ በላይ ነው (2x) አመሰግንሃለው (6x) እንደ ባለማዕረግ ሰው ተመልክተኸኝ የማይገባኝን ክብርን ሰጥተኸኝ የርስትህ ተካፋይ የአንተው አደረከኝ ለዚህ ልታበቃኝ ታዲያ እኔ ማን ነኝ (2x) አዝ፦ ስለተደረገልኝ በጐነት ጨምሬ ምለው ምንድን ነው ጨምሬ ምለው ምንድን ነው (2x) ሥራህ ከአእምሮዬ በላይ ነው (2x) አመሰግንሃለው (6x) ማዕበሉ በዝቶብኝ እኔን ሲያንገላታኝ ጌታ ኢየሱስ አልኩኝ ሥምህን ጠራሁኝ እጅህን ዘርግተህ በፀናችው ክንድህ ታደከኝ አዳንከኝ ተባረክ ልበልህ (2x) አዝ፦ ስለተደረገልኝ በጐነት ጨምሬ ምለው ምንድን ነው ጨምሬ ምለው ምንድን ነው (2x) ሥራህ ከአእምሮዬ በላይ ነው (2x) አመሰግንሃለው (6x) የተገለጠውን ፍቅርህን እያየሁ እንዳልተቀበለ እንዴት እሆናለሁ ምህረት ማዳንህን ሁሌ አወራለሁ አምላኬ እንደ አንተ ፍፁም አምላክ ማነው (2x) አዝ፦ ስለተደረገልኝ በጐነት ጨምሬ ምለው ምንድን ነው ጨምሬ ምለው ምንድን ነው (2x) ሥራህ ከአእምሮዬ በላይ ነው (2x) አመሰግንሃለው (6x) በለቅሶ ሸለቆ በወሰንከው ስፍራ ጌታ ኢየሱስ ለእኔ በረከትህ በዛ ከኃይል ወደ ኃይል ያሸጋገርከኝ ሁሉ በአንተ ሆነልኝ ኧረ ምን ጐደለኝ (2x) አዝ፦ ስለተደረገልኝ በጐነት ጨምሬ ምለው ምንድን ነው ጨምሬ ምለው ምንድን ነው (2x) ሥራህ ከአእምሮዬ በላይ ነው (2x) አመሰግንሃለው (6x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection