ምንም በሌለበት ጭው ባለው በረሃ አጋር ከነልጇ ወደዚያ ተሰዳ ተደፍታ ስታለቅስ ምርር ያለ ለቅሶ ምንጭ አፈለቀላት እግዚአብሔር ደርሶ [1] ይደርሳል እግዚአብሔር ይደርሳል ይደርሳል የተጠማ ያያል ምንጭን ያፈልቅና አሜን ያሳርፋል (2x) መጠጥ እነደጠጣች ስካር እንደያዛት ካህኑ ኤሊ እንኳን ሃናን ጠረጠራት እርሷ ግን የውስጧን ችግሯን ለሚያውቀው ተናገረችና ልቧ በእርሱ ፀና [2] ይረዳል እግዚአብሔር ይረዳል ይረዳል የውጥን ይረዳል የተዘጋን ከፍቶ በልጅ ይባርካል (2x) እስራኤላውያኖች ቀንበር ከብዶባቸው የግብፅ ባርነት እጅግ ሰልችቷቸው ጮሁ ወደ እግዚአብሔር እንዲታደጋቸው እጁን ዘረጋና ነፃ አወጣቸው [3] ያወጣል እግዚአብሔር ያወጣል ያወጣል ነፃነት ይሰጣል ከእስራት ይፈታል አሜን ያሳርፋል (2x) እመሰክራለሁ በሕይወቴ አይቻለሁ ንብ ማርን እንዲከብ ተከብቤ ሳለሁ በጨነቀኝ ጊዜ አምላኬን ስጣራ እርሱም ደረሰልኝ ጨለማዬም በራ ያበራል እግዚአብሔር ያበራል ያበራል ጨለማን ይገፋል በድንቅ ይደርስና አሜን ያሳርፋል (2x) ቀን በደመና አምድ ለሊትም በእሳት አቤት የእኔ ጌታ መምራትን ሲያውቅበት ላዘነው መፅናናት ለደካማው ብርታት ይሄ ነው አምላካችን እስኪ ዕልል በሉለት ይብዛለት አሁንም ይብዛለት ይብዛለት ምሥጋና ይብዛለት አሜን ለአምላካችን ክብር ይሁንለት (2x)