አዝ፦ ሰው ሁሉ ዓለሙን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ባያድን ምን ይጠቅመዋል (4x) የሰው ድካሙ ለሥጋ ሆኖአል አይ ነፍሱ ግን በርሃብ ጠውልጓል ያከማቻውም ለሌላ ይሆናል የደከመበትን ሳይበላ ይቀራል (2x) አዝ፦ ሰው ሁሉ ዓለሙን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ባያድን ምን ይጠቅመዋል (4x) ፈጣሪህን አስብ በጉብዝናህ ወራት ኃይል ከአንተ እርቆ ሳይጥልህ ጉልበት ትእዛዙን ጠብቅ ፍራ እግዚአብሔርን ነፍስህ ሳይመለስ ሥጋ ወደ አፈር (2x) አዝ፦ ሰው ሁሉ ዓለሙን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ባያድን ምን ይጠቅመዋል (4x) በሕይወት ዘመንህ የሚሻልህን እንዳትረዳው ጋርዶ የያዘህን ዓይንህ ይገለጥ ከንቱ ነው ሁሉ በዚህ ዓለም ላይ ያለው በሙሉ በሕይወት ዘመንሽ የሚሻልሽን እንዳትረጂው ጋርዶ የያዘሽን ዓይንሽ ይገለት ከንቱ ነው ሁሉ ከኢየሱስ ውጭ ያለው በሙሉ አዝ፦ ሰው ሁሉ ዓለሙን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ባያድን ምን ይጠቅመዋል (4x)