አዝ፦ ወንድሜ ንቃ አትተኛ (2x) ጌታ ሊመጣ ቀርቧል ስዓቱ የመገለጡ (2x) ጌታ እንደ ሌባ ይመጣልና ቀን . (1) . አታውቅምና ስለዚህ ንቃ መብራትህ ይብራ በፍጻሜው ቀን እንዳትፈራ አዝ፦ ወንድሜ ንቃ አትተኛ (2x) ጌታ ሊመጣ ቀርቧል ስዓቱ የመገለጡ (2x) ስሙን በመፍራት ለሚኖሩት የጽቅድ ጸሃይ ይወጣል በእውነት እምላክህን ፍራ ጠብቀው ተግተህ በክብር ሲገለጥ እንዳያፍርብህ አዝ፦ ወንድሜ ንቃ አትተኛ (2x) ጌታ ሊመጣ ቀርቧል ስዓቱ የመገለጡ (2x) ከማያምኑ ጋር ህብረት አይኑርህ በማይመችህ መንገድ አትሂድ ይልቅ ዘመኑን መርምር አጥብቀህ በከንቱ አንዳያልፍ ጐልማሳነትህ አዝ፦ ወንድሜ ንቃ አትተኛ (2x) ጌታ ሊመጣ ቀርቧል ሰዓቱ የመገለጡ (2x) እርሱን ከሚሉ ጋር ደስ ይበልህ ከሰው ሁሉ ጋር ሰላም ይኑርህ እጅጉን ንቃ ጊዜው ተቃርቧል አሜን ይሆናል በርግጥ ይመጣል አዝ፦ ወንድሜ ንቃ አትተኛ (2x) ጌታ ሊመጣ ቀርቧል ስዓቱ የመገለጡ (2x) ጌታ ሊመጣ ቀርቧል ስዓቱ የመገለጡ ኢየሱስ ሊመጣ ቀርቧል ስዓቱ የመገለጡ