Song Lyrics

ለእኔ ያለህ ፍቅር

Redda Abraham
Altilihim altewuhim
አዝ፦ ለእኔ ያለህ ፍቅር ጌታ ልዩ ነው ለእኔ ያለህ ፍቅር ኢየሱስ ልዩ ነው አይምሮን ያልፋል እጅግ ይበዛል እንዴት ሊነገር ይችላል በምን ሊገለጽ ይችላል ለእኔ ያለህ ፍቅር ልዩ ነው መስቀል ተሸክመህ ደፋ ቀና ብለህ በፈጠርከው ፍጥረት እየተንገላታህ እጅጉን ተንቀህ በጣምም ተዋርደህ እኔን አድነሃል ይግነን ታላቅ ስምህ (2x) አዝ፦ ለእኔ ያለህ ፍቅር ጌታ ልዩ ነው ለእኔ ያለህ ፍቅር ኢየሱስ ልዩ ነው አይምሮን ያልፋል እጅግ ይበዛል እንዴት ሊነገር ይችላል በምን ሊገለጽ ይችላል ለእኔ ያለህ ፍቅር ልዩ ነው ለአይምሮ በሚክብድ በዘግናኝ ሁኔታ እጅህና እግርህ በሚስማር ተመታ ያለ እንዳች ርህራሄ ኢየሱስ በጭካኔ ግፍ አደረሱብህ ተሰቃየህ ለእኔ (2x) አዝ፦ ለእኔ ያለህ ፍቅር ጌታ ልዩ ነው ለእኔ ያለህ ፍቅር ኢየሱስ ልዩ ነው አይምሮን ያልፋል እጅግ ይበዛል እንዴት ሊነገር ይችላል በምን ሊገለጽ ይችላል ለእኔ ያለህ ፍቅር ልዩ ነው ከወንበዴዎች ጋር ሰቀሉህ ኢየሱስ ከላይ የወረድህ ሳለህ የዓለም ንጉስ ሆምጣጤም አጠጡህ ጨከኙ በብዙ ጌትነትህ የታል እያሉ እያፌዙ (2x) አዝ፦ ለእኔ ያለህ ፍቅር ጌታ ልዩ ነው ለእኔ ያለህ ፍቅር ኢየሱስ ልዩ ነው አይምሮን ያልፋል እጅግ ይበዛል እንዴት ሊነገር ይችላል በምን ሊገለጽ ይችላል ለእኔ ያለህ ፍቅር ልዩ ነው በእንጨት ተሰቅለህ እንደ መርገም ሰው ለጠላቶችህ ማለድኽ ፍቅርህ ሰፊ ነው ተፈጸመም አልህ ነፍስህን ሰጠህ ለኔ ከፍ በል ተባረክ ዘላለም መድህኔ (2x) አዝ፦ ለእኔ ያለህ ፍቅር ጌታ ልዩ ነው ለእኔ ያለህ ፍቅር ኢየሱስ ልዩ ነው አይምሮን ያልፋል እጅግ ይበዛል እንዴት ሊነገር ይችላል በምን ሊገለጽ ይችላል ለእኔ ያለህ ፍቅር ልዩ ነው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection