Song Lyrics

አልጥልህም አልተውህም

Redda Abraham
Altilihim altewuhim
በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም ከሙሴ ጋር እንደሆንኩ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ አልጥልህም አልተውህም አልጥልህም አልተውህም ከሙሴ ጋር እንደነበርኩ ከአንተ ጋርም እሆናለሁ ብቻ በርታ ጽና ልጄ ሁሉን መልካም አደርጋለሁ ምንም ነገር ዓይነካህም እርግማን አይደርስብህም በጠላት ላይ ትጫማለህ ዘንዶ እባቡን ትረግጣለህ አዝ፦ እንዲህ ላልከኝ ለአምላኬ እሰግዳለሁኝ ተንበርክኬ (2x) አልጥልህም አልተውህም ላልከኝ ለዘላለም ከአንተ ጋር ነኝ ላልከኝ አንተ እግዚአብሔር የእስራኤል ተስፋ እስግዳለሁ ዙፋንህ ይንሰራፋ አንተ እግዚአብሔር የሕያዋን ተስፋ አስግዳለሁ ዙፋንህ ይንሰራፋ ለዘላለም ኤልሻዳይ ነህ ና በፊቴ ተመላለስ የገባሁልህን ተስፋ አምጥቻለሁና ለአንተ በዚህ ስለዚህ አትጠራጠር ጸንተህ ቁም በእኔ ተማምነህ የማልጥል የማልተው አምላክ አለሁ እኔ በአጠገብህ አዝ፦ እንዲህ ላልከኝ ለአምላኬ እሰግዳለሁኝ ተንበርክኬ (2x) አልጥልህም አልተውህም ላልከኝ ለዘላለም ከአንተ ጋር ነኝ ላልከኝ አንተ እግዚአብሔር የእስራኤል ተስፋ እስግዳለሁ ዙፋንህ ይንሰራፋ አንተ እግዚአብሔር የሕያዋን ተስፋ አስግዳለሁ ዙፋንህ ይንሰራፋ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ሊቋቋሙህ እንዳይችሉ ጠላቶችህን መታለሁ በፊት ለፊትህ ጥላለሁ በክንዶቼ ትያዛለህ ብቻ ታመን ትድናለህ ለዘላለም የእኔ ነህ ከእቅፌ ማን ሊያወጣህ አዝ፦ እንዲህ ላልከኝ ለአምላኬ እሰግዳለሁኝ ተንበርክኬ (2x) አልጥልህም አልተውህም ላልከኝ ለዘላለም ከአንተ ጋር ነኝ ላልከኝ አንተ እግዚአብሔር የእስራኤል ተስፋ እስግዳለሁ ዙፋንህ ይንሰራፋ አንተ እግዚአብሔር የሕያዋን ተስፋ አስግዳለሁ ዙፋንህ ይንሰራፋ እንደቃሌ እንዲሁ ነኝ አደርጋለሁ ከቶ አልዋሽም የተናገርኩትን ሁሉ ፈጽማለሁ እንድ አይቀርም ከእኔ በቀር አምላክ የለም ማንም በምድር በሰማይ ብቻዬን ነኝ አልለወጥ ለዘላለም ኤልሻዳይ አዝ፦ እንዲህ ላልከኝ ለአምላኬ እሰግዳለሁኝ ተንበርክኬ (2x) አልጥልህም አልተውህም ላልከኝ ለዘላለም ከአንተ ጋር ነኝ ላልከኝ አንተ እግዚአብሔር የእስራኤል ተስፋ እስግዳለሁ ዙፋንህ ይንሰራፋ አንተ እግዚአብሔር የሕያዋን ተስፋ አስግዳለሁ ዙፋንህ ይንሰራፋ እስራኤልን ትመራለህ ዮርዳኖስን ትከፍላለህ ከግራ ቀኝ አለሁ እኔ ታወጣለህ ታገባለህ ከአንተ ጋራ እንዳለሁኝ በህዝቡ ዘንድ ይታወቃል ዘመንህን ባርኬያለሁ ገለአድን ትወርሳለህ ከአንተ ጋር እንዳለሁኝ በህዝቡ ዘንድ ይታወቃል ዘመንህን ባርኬያለሁ ክብሬ በላይህ ይታያል አዝ፦ እንዲህ ላልከኝ ለአምላኬ እሰግዳለሁኝ ተንበርክኬ (2x) አልጥልህም አልተውህም ላልከኝ ለዘላለም ከአንተ ጋር ነኝ ላልከኝ አንተ እግዚአብሔር የእስራኤል ተስፋ እስግዳለሁ ዙፋንህ ይንሰራፋ አንተ እግዚአብሔር የሕያዋን ተስፋ አስግዳለሁ ዙፋንህ ይንሰራፋ አልጥልህም አልተውህም ላልከኝ ለዘላለም ከአንተ ጋር ነኝ ላልከኝ አንተ እግዚአብሔር የእስራኤል ተስፋ እስግዳለሁ ዙፋንህ ይንሰራፋ አንተ እግዚአብሔር የቅዱሳን ተስፋ እስግዳለሁ ዙፋንህ ይንሰራፋ አንተ እግዚአብሔር የኢትዮጵያ ተስፋ እስግዳለሁ ዙፋንህ ይንሰራፋ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection