አዝ፦ መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴ እንዳይላላ ሃሌሉ ሃሌሉ ሃሌሉያ (4x) የቀራንዮን በግ ኢየሱስን ይዣለሁ በሁለንተናዬ ላይም ሾሜሃለሁ አልፈራም አልሰጋም ወጥቼ እገባለሁ ዓለምን ሰይጣንን ስልጣኑን ክጃለሁ አዝ፦ መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴ እንዳይላላ ሃሌሉ ሃሌሉ ሃሌሉያ (4x) ይህ የመስቀሉ ቃል በዓለም ለሚኖሩት ከሞኝነት ውጭ አልሆነም ለሕይወት ለእኔ ለምድን ግን በርታት ሆኖልኛል የተሰራው ስራ ሕያው ሰው አርጐኛል አዝ፦ መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ ሃሌሉ ሃሌሉ ሃሌሉያ (4x) ሁሉን ፈጽማችሁ በፊቱ ለመቆም የእምነትን ጋሻ ታጠቁ ልበሱ የሚልን የድል ቃል ይዤ ልትጋ ልሩጥ ጠፍቶ ከሚያጠፋ ከዚህ ዓለም ለማምለጥ አዝ፦ መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ ሃሌሉ ሃሌሉ ሃሌሉያ (4x) ስለዓለም ሃጥያት ነፍሱን የሰጠውን መከራና ስቃይ የተቀበለውን እገሰግሳለሁ ታምኜው ከልቤ እያገለገልኩት በፍፁም ሃሳቤ አዝ፦ መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ መስቀሉ ከፊቴ ነው ዓለምም ከኋላ ኢየሱስን ይዣለሁ ጉልበቴን እንዳይላላ ሃሌሉ ሃሌሉ ሃሌሉያ (4x)