Song Lyrics

አቤቱ በዘመናት

Redda Abraham
Altilihim altewuhim
አዝ፦ አቤቱ በዘመናት በአመታት መካከል ብቻህን ስራህን ሰርተህ ትኖራለህ ከብረህ ደምቀህ ትኖራለህ ከብረህ ደምቀህ (2x) በዘመን በአመታት ስራህን እየሰራህ የሚቃወምህ ሳይኖር ክንድህን እየገለጥክ ልጆችህን ከድል ወደ ድል እያሸጋገርካቸው የጠላታቸውን ሰፈር ይታያል . (1) . ወርሰው አዝ፦ አቤቱ በዘመናት በአመታት መካከል ብቻህን ስራህን ሰርተህ ትኖራለህ ከብረህ ደምቀህ (2x) ፈርዖን ለዘመናት ሲያስጨንቅ ልጆችህን ሕዝቤን ልቀቅ ስትለው ትዕቢት አርጐ ሲፋንን በመጨረሻ ጌታ የግብጽን በኩር ገድለህ ህዝብህን ነጻ አውጥተህ ጠላትን . (1) . ጥለህ አዝ፦ አቤቱ በዘመናት በአመታት መካከል ብቻህን ስራህን ሰርተህ ትኖራለህ ከብረህ ደምቀህ (2x) ሁልጊዜ ሃሳብህን የልብህንም ፈቃድ ታከናውነዋለህ በምትወደው መንገድ በጐና ደስ የሚያሰኝ ግሩምና ድንቅ ነው አምላካችን እግዚአብሔር አንተ የምታደርገው አዝ፦ አቤቱ በዘመናት በአመታት መካከል ብቻህን ስራህን ሰርተህ ትኖራለህ ከብረህ ደምቀህ (2x) ክብርህ ሰማያትንና ምድርን ሁሉ ሸፍኗል በምክርህ በመንገድህ አንተን ማን ያክልሃል ውበትህ ከፀሐይ ይልቅ እጅግ እጅግ ይደምቃል ፍጥረት በሙሉ ይህን እያየ ያከብርሃል አዝ፦ አቤቱ በዘመናት በአመታት መካከል ብቻህን ስራህን ሰርተህ ትኖራለህ ከብረህ ደምቀህ ትኖራለህ ከብረህ ደምቀህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection