Song Lyrics

እምቢ ብዬ

Redda Abraham
Altilihim altewuhim
እምቢ ብዬ ሰይጣንን ከድቼው መጥቻለሁ በኢየሱስ ጸንቼ ለመቆም መርጫለሁ አልመኝም አንዳች አልፈልግም በሕይወቴ ይበቃኛል የመስቀሉ ወዳጅ መድህኔን እዤ አዝ፦ ከእርሱ ውጪ አልመኝ አንዳች ነገር አያምረኝ መጥቻለሁ በፍቅር ለዘላለም ለመኖር (2x) ብዙ ወዳጅ ማከማቸት ከንቱ ነው ያጠፋል ለሁለት ጌቶች መገዛትም ደግሞ ሁሉን ያሳጣል እኔስ በቃኝ እንድ ወዳጅ አለኝ ኢየሱሴ በዚች ዓለም የተጐሳቆለው ስለነፍሴ አዝ፦ ከእርሱ ውጪ አልመኝ አንዳች ነገር አያምረኝ መጥቻለሁ በፍቅር ለዘላለም ለመኖር (2x) ፍቅሩ የእውነት የማይለዋወጥ እጅግ የጸና በምህረቱ ሰውን የሚያቆመው ለምሥጋና ዛሬ ይኽው እኔም ተመርጨ ዕጣው ደርሶኝ ወደቤቱ መጣሁኝ ለክብሩ ቅኔን ልቀኝ አዝ፦ ከእርሱ ውጪ አልመኝ አንዳች ነገር አያምረኝ መጥቻለሁ በፍቅር ለዘላለም ለመኖር (2x) የዚህን ዓለም ብልጽግና ክብር ላልመኘው ጊዜያዊውን የሚያልፈውን ነገር ላልፈልገው ወስኛለሁ መርጫለሁ ጌታ ይሻለኛል ለዘላለም . (1) . አዝ፦ ከእርሱ ውጪ አልመኝ አንዳች ነገር አያምረኝ መጥቻለሁ በፍቅር ለዘላለም ለመኖር (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection