አዝ፦ በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ በቸርነትህ ዘመናትን ታቀናጃለህ ጌታ ኤልሻዳይ ነህ ኢየሱስ ኤልሻዳይ ነህ (2x) ምድራችንን ጐበኘሃት ምህረትን ለእርሷ አደረግህ ብልጽግናዋን አበዛህ ምግቧን አዘጋጅተህ ሰጥተህ . (1) . በማስተካከል እውነት እያለስለስካት ቡቃያውን በመባረክ መልካም ፍሬን አጠገብካት (2x) አዝ፦ በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ በቸርነትህ ዘመናትን ታቀናጃለህ ጌታ ኤልሻዳይ ነህ ኢየሱስ ኤልሻዳይ ነህ (2x) ከክብርህ ባለጠግነት ነፍሳችንን እያጠገብክ እስከ ሺ ትውልድ በሆነው በረከትህ እየባረክ ሁሉን ለእኛ ሰጥተኸናል የረገጥነውን ወርሰናል በስምህ ስልጣን በኃይልህ ሮሆቦት አሜን ሰርተናል (2x) አዝ፦ በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ በቸርነትህ ዘመናትን ታቀናጃለህ ጌታ ኤልሻዳይ ነህ ኢየሱስ ኤልሻዳይ ነህ (2x) የምድርን አፈር ባርከኸው ሰብልን ይሰጣል ዛሬ ጠግበን ረክተን እንኖራለን ለቅሷችን ሆኗል ዝማሬ ወራት አመት ዘመናትን ለልጆችህ ተሰጥተዋል ኤልሻዳይ ንጉሥ አንተ ነህ ሁሉን አቀዳጅተኸናል (2x) አዝ፦ በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ በቸርነትህ ዘመናትን ታቀናጃለህ ጌታ ኤልሻዳይ ነህ ኢየሱስ ኤልሻዳይ ነህ (2x) የምድረበዳ ተራሮች በመንፈስ እውነት ረክተዋል ኮረብቶችም በደስታ በስምህ ሀይልን ታጭቀዋል የማሰማሪያ ቦታዋች በመንጐቹ ውበት ለበሱ ሸለቆ እህል ተሞልቶ ክበር/ድመቅ ይልሃል ንጉሡ (2x) አዝ፦ በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ በቸርነትህ ዘመናትን ታቀናጃለህ ጌታ ኤልሻዳይ ነህ ኢየሱስ ኤልሻዳይ ነህ (2x)