አዝ፦ ጌታ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (2x) ጌታ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (2x) ቸርነትህ ምህረትህ በሕይወት ዘመኔ ስለሚጠብቁኝ በመሆን ከጐኔ አልጠፋሁም ኢየሱስ አለሁኝ በቤትህ ስዘምር እኖራለሁ ለታላቁ ስምህ አዝ፦ ጌታ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (2x) ጠላቴ ሊያጠፋኝ ጦሩን ሲወረውር ከግድግዳ ጋርም እኔኑ ሊያጣብቅ ነገር ግን አልሆነም ምህረትህ ቀደመ የዲያብሎስ ሃሳብ እቅዱ ባከነ አዝ፦ ጌታ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (2x) በምህረትህ ብዛት ቤትህ እገባለሁ አምልኮ ዝማሬ ስግደት እየሰጠሑ ገናም እኖራለሁ ስለምትጠብቀኝ እስከ ዓለም ፍጻሜ ሰለማትተወኝ አዝ፦ ጌታ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (2x) አግዚአብሄር ታላቅ ባለብዙ ምህረት ልጅህ ስላረከኝ በብዙ ቸርነት እኔም በዝማሬ ምህረትህን አነግራለሁ እስከምትወስደኝ አገለግላለሁ አዝ፦ ጌታ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (2x) በልዑል መጠጊያ ሁሉን በምትችለው ባንተ ስለምኖር ምህረትህ በበዛው የሚያስፈራኝ የለም ከጠላትህ መንደር አንተ ስለጣልከልኝ ወደ ጥልቁ ባሕር አዝ፦ ጌታ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (2x) ኢየሱስ ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (2x) ልዑል ሆይ ምህረትህ እንዲሁም ጥበቃህ ደግሞም ቸርነትህ በእኔ ላይ በዝተዋል (2x)