Song Lyrics

ከእግርህ ስር

Rahel Wendwesen
Special Edition
የሚያስፈልገው ጥቂት ወይም አንድነገር እርሱም በፊትህ መሆን ከእግሮችህ ስር ማይወሰድብኝ መልካም ዕድል የማስቀድመው ማልለው ቸል የአንደበትህን ቃል መስማት ማዳመጥ እርፍ ብዬ በድምፅህ መመሰጥ ከእግርህ ስር እንደመሆን ያለ ከፍታ የለም ካንተ ጋር እንደማውራት ያለ ደስታ የለም ቃልህን እንደመስማት ያለ እረፍት የለም በክብርህ እንደመቆየት ያለ ክብር የለም (በክብርህ ውስጥ እንደመቆየት ያለ ክብር የለም) መች ሆነና ያለ ልክ ብክነቴ ቀልብህን የሚስብ መች ሆነና ረብ የሌለው ሩጫ አንተን ፈገግ ሚያስብል መች ሆነና ጉድ ጉድ ማለቴ ቀልብህን የሚስብ መች ሆነና የሰበብ መዓቴ አንተን ፈገግ ሚያስብል ከየትኛውም ነገሬ በፊት አስቀድመህ ትፈልገኛለህ ለአባትና ለልጅ ፍቅራችን ትልቅ ዋጋ አለህ ከየትኛውም ነገሬ በፊት ቀድመህ እኔን ትፈልገኛለህ ለአባትና ለልጅ ፍቅራችን ትልቅ ዋጋ አለህ እጅጉን ናፍቀሀኝ ስመጣ ቸኩዬ ጥድፍ ጥድፍ እያልኩ ወደ መሰዊያዬ በቀጠርኩህ ሰዓት ተገኝተህ ሳትንቀኝ ልጄ የማወጋሽ ብዙ አለኝ ስትለኝ ልቤ ፈነደቀ በደስታ ቀለጠ ከድካሜ በላይ ፍቅርህ እጅግ በለጠ ትልቅ ሆነህ ሳለህ አባቴ የኔም ድምፅ ናፍቆሀል ከታናሿ ከእኔ ይገርማል! ቁም ነገር ይዘሀል ከእግርህ ስር እንደመሆን ያለ ከፍታ የለም ካንተ ጋር እንደማውራት ያለ ደስታ የለም ቃልህን እንደመስማት ያለ እረፍት የለም በክብርህ ውስጥ እንደመቆየት ያለ ክብር የለም ለኔ ግን ወደ አንተ መቅረብ ይሻለኛል ወደ ጉያህ ወደ ደረትህ ብጠጋ ይበጀኛል ካንተ ጋር ያለኝን ህብረት ምንም አይተካውም ሳላገኝህ መዋል ማደር በፍፁም አልችልም
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection