Song Lyrics

ገስፀኝ

Rahel Wendwesen
Kene Ayidelem
በንግስናው ወራት በአይኑ ተመኘ ለልቡ ፍላጎት ደስታ ተማረከ ጌታ ማይወደውን በደልን ፈፀመ በአምላኩም ፊት ስራው እጅግ ክፉ ሆነ ተው ዳዊት ተመለስ×2 እያለ በአድራሻው የአምላክ ድምፅ መጣ ከወደቀበት ሊያነሳው ልቡን ከፍቶ ኖሮ ይሄ በጎ መልካም ባሪያ ከጥፋቱ ድኖ አድሮዋል በአምላኩ ጉያ የወደቀን ማንሳት ኢየሱስ ልማድህ በደለኛውን መማርህ መክረህ መመለስህ ምኞቴን ስከተል ውድቀቱ እንዳይቀድመኝ ለእኔም የምክርህን ፈጥነህ ተናገረኝ ተናገረኝ እሰማሀለሁ ገስፀኝ እመለሳለው ቃልህ የሚመልስ ነው ድምፅህ የሚያሳርፍ ነው ምክርህ የሚያቀና ነው ዘለፋህ የሚጠግን ነው አባት ልጁን እንዲገስፅ ገስፀኝ እገሰፃለሁ መክሮ ዘልፎትም እንዲመልስ ምከረኝ እመከራለሁ ተይ ተመለሽ ልጄ በለኝ ስርዓትህን አስተምረኝ ካንተ የሚያውቅልኝ ማን አለኝ ካንተ የሚቀርብ ማንም የለኝ ካንተ ወዲያ ማንን ላገኝ ገስፀኝ እሰማሀለሁ ተናገረኝ አደምጥሀለሁ ቃልህ የሚመልስ ነው ድምፅህ የሚያሳርፍ ነው ምክርህ የሚያቀና ነው ዘለፋህ የሚጠግን ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection