በጥፋቱ ምክንያት ከአባቱ ቤት የወጣው አታላይ የተባለውን ያዕቆብ እስራኤል አልከው ህዝቤ ብለህ ጠራሀው የብዙዎች አባት አደረከው የቀድሞ ስሙን ቀይረህ መባረክን ባረከው የእኔም ታሪክ እንደዚሁ ነበር ውዳቂ ነበርኩኝ ህይወቴ ጠረን የሌለው ቀንበር የከበደብኝ በድቅድቅ ጨለማ ያለው የሰማዩ ብርሃን በህይወቴ እንዲበራ በእውነተኛው መንገድ ነፍሴን ልትመራ ምህረትህ በዛና ሆንክልኝ መዳን ከተፍ አልክልኝና ቀየርከው ስሜን መመረጤ ከምንም በላይ ነው መመረጤ ዕድለኛ ነኝ ስለማገለግለው ምርጤ ነሽ ብሎኛል መመረጤ ከምንም በላይ ነው መመረጤ ባርያዎችህን አሳዳች አንገላች የነበረው ጳውሎስን አግኝተኸው ህይወቱን ቀየርከው አሳዳጅ መሆኑ ቀረና ታማኙ ባሪያዬ ተባለ ዋና በሆነ በሱ ላይ ምህረትህ እጅጉን አየለ የኔም ታሪክ እንደዚሁ ነበር ግን ተሸነፍኩ ተረታው ባንተ ፍቅር ተመስገን ተወደስ