አባ አባ ብዬ እንድጮህ የልጅነት መንፈስ ሰጠኸኝ ወደ ፀጋህ ዙፋን ፊት በእምነት እንድቀርብ ድፍረት ሆንከኝ ልጄ ብለህ ልትጠራኝ ያላፈርክብኝ አንተ አባቴ ነህ ዳግም የወለድከኝ አባቴ ነህ በድካሜ የራራህልኝ አባቴ ነህ ዘላለም ልጅህ ያደረከኝ አባቴ ነህ ገስፀህ የምትመልሰኝ አባቴ ነህ ሚያሰፈልገኝን የምታውቅልኝ አባትዬ ተንከባክበህ አሳደከኝ አባብዬ እንደ አይን ብሌን ተጠነቀክልኝ አባት አለኝ አፉን እንዳልፈታ እንደ ህፃን ልጅ እየተኮላተፍኩ አባ ልበል እንጂ ይገባሀል ንግግሬ ግራ አይገባህ መንተባተቤ ይልቅ የልቤን ትረዳለህ ካሰብኩትአብልጠህ ታደርጋለህ