ክብር ይሁንልህ ×3 ሞገስ ይደረብልህ ×3 ስላነሰ አይደለም ማበዛው ምስጋና ስለሚገባህ ነው ስለሆንክ ገናና ግርማህ የሚያስፈራ ዕፁብና ድንቅ ክብሬን ልጣልና አንተን ላደናንቅ ያንስብሀል ከዚህም በላይ ልሁንልህ በፊትህ ወድቄ ቅዱስ ልበልህ ምስጋናዬን ላብዛልህ አምልኮዬ ያርግልህ የተገባህ ስለሆንህ እልልታዬን ላምጣልህ ሀሌሉያ×6 ክብርህን ያዪ ሁሉ ከእግርህ ስር ተንቀጠቀጡ ከመናገር ተቆጠቡ ዝም አሉ ስለ አንተ የሚሉትን አጡ እኔም ተደምሜ ተደንቄ ቃላት አጥረውኛል ትልቅነትህን ሳስብ እጅግ ይገርመኛል ከአለቆች በላይ ነህ ከስልጣናት በላይ ከምልህም በላይ ነህ የሁሉ የበላይ ሀሌሉያ×6 ከመገረም በላይ ምን አለ ሌላ ግርምት ከመደነቅ በላይ ምን አለ ሌላ ድንቀት ከሌላው በላይ ምን አለ ሌላ ቃላት ×2 ቢኖር ምን አለ ከቢኖርም ሌላ ከሌላውም ሌላ ከዚያም ሌላ ሀሌሉያ×8