በበደሌ ምክንያት ሙት ነበርኩኝ በሀጥያቴም ደግሞ ኩነኔ ነበረብኝ ግን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሳ አባቴ በፀጋው በእምነት አዳነኝ ኢየሱሴ ከኔ አይደለም ከስራዬ ከበጎነት ከመልካምነቴ ነገር ግን ለመልካም ስራ ተፈጥሬአለው ትልቅን ዋጋ ከፍሎልኝ ህይወት አግኝቻለው ነገር ግን በምህረቱ ባለጠጋ ስለሆነ የቁጣ ልጅ የነበርኩትን እኔን አዳነ ለኔ ብሎ ወደ ምድር ወርዶ ለኔ ብሎ ራሱን አዋርዶ ለኔ ብሎ መስቀል ላይ ሆኖ ለኔ ብሎ ደሙን አፍስሶ ፍቅሩ የበዛልኝ ልጁ ተብያለው በኢየሱስ ቤዛነት ህይወት አግኝቻለው ማን እንዲህ አሰበልኝ ከአእምሮ በላይ ነው ዉለታዉ የበዛ ፍቅሩ እጅግ ጥልቅ ነው አንዴ አመለጥኩ ከባርነት ከግዞት ቤት ሞት ካለበት እዳዬ ሁሉ ተሰርዟል ታላቅ መዳን ለኔ ሆኗል ምስጋናዬ ይድረሰው አምልኮዬ ይድረሰው ዝማሬዬ ይድረሰው አድናቆቴ ይድረሰው በእርሱ ነው መዳኔ በእርሱ ነው መኖሬ በኢየሱስ ነው መትረፌ የዘላለም ህይወት ማግኘቴ