Song Lyrics

ልፍስፍስ ይላል

Rahel Wendwesen
Special Edition
ልፍስፍስ ይላል ይዝላል አካሌ የተወደድኩበትን መውደድ ሲያስበው ልቤ አንደበቴ ቋንቋ ያጥረዋል ንግግር ያቆማል በእንባ ጠብታ አይኔ የውስጤን ያወራል ፍቅርህ አይሎብኛል ፍቅርህ ፍቅርህ አይሎብኛል ፍቅርህ ኢየሱሴ ፍቅርህ ልቆብኛል ኢየሱሴ ፍቅርህ ገኖብኛል ፍለጋ ምርጥ ስንኝ ቃላት ላገጣጥም የውስጤን ባይገልፀው ባይጠጋጋውም ፊደላት ሰነፉ መቆም አቃታቸው የኢየሱሴ ፍቅር ተግባር ሆኖባቸው ከቃል አልፎባቸው እጄም ልፋ ብሎት ደጋግሞ ቢሞክር ጣቴም የአቅሙን ቢያደርግም ጫር ጫር ገና ከጅምሩ ብዕሬ ቀለሙ አለቀ ንፁሁ ወረቀት በስርዝ ተጨመላለቀ ኢየሱሴ ፍቅርህ ልቆብኛል ኢየሱሴ ፍቅርህ ገኖብኛል ዘመኔን ጨርሰው አንተው ተጠቀመው ህይወቴን ኑርበት እንዳሻህ ስራበት የሰጠኸኝ ዕድሜ ብቻውን አይበቃ ለውለታህ ምላሽ ብዘምር ቀንም ሆነ ማታ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection