የባከኑትን እነዚያን ጊዜያቶች ልክስህ እፈልጋለው አልቀልድም በሰጠኸኝ እድሜ ያኖርከኝ በምክንያት ነው በህይወቴ አንተን ልካስ የልቤ መሬት ለቃልህ ይታረስ በኑሮዬ አንተን ልካስ አሮጌው ይቀየር በአዲስ እንዲሁ በዋዛ ቀናት ተቆጠሩ ይብቃኝ ብርሃን ሳልሆን ውሎና አዳሩ አጥንቴን ደግፈህ ጉልበቴን በእጅጉ ካገዝከው አልረፈደም ዛሬም አባቴ አስደስትሀለው መንፈስህ ከረዳኝ ድካሜን ካገዘ ብርሃን እስካየሁ አይኔ ካልፈዘዘ እጆችህ እጄን አሁንም አጥብቀው ከያዙ ሀይሌ እነደገና ይታደሳል በእጥፍ በብዙ እንደ ሰማይ ምድር ሀሳቤ ከሀሳብህ እጅጉን እርቋል እግሬ ከመንገድህ ዛሬ ግን ምረሀኝ ህይወቴ ይበርታ ይጠንክር በቀረልኝ እድሜ በሙሉ አንተን እንዳስከብር