የአንድያ ልጅህ በእንጨት መስቀል ላይ መሰቀል መሞት በዚህ አለም ሚዛን ነው ለሚጠፉት እጅግ ሞኝነት እግዚአብሔር የአንተ ጥበብ የፍቅርህ ጥጉ ኢየሱስ ነው እግዚአብሔር የአንተ ጥበብ የፍቅርህ ጥጉ ኢየሱስ ነው የአንተ ጥበብ ኢየሱስ ሊበራልኝ ቀርቶ የሰው ጥበብ ላይ እንኳ አልደረስኩም ከቶ በስብከት ሞኝነት በተቀበልኩህ ቀን መጨረሻው ገባኝ የጥበብህ እርከን በስብከት ሞኝነት ባንተ አምኜ አባቴ ሆንክና ቀረው ልጅህ ሆኜ ለዚህ ድንቅ ማዳንህ ልቀኝ ላክብርህ ለዚህ ድንቅ ስጦታህ ልቀኝ ላምልክህ በተመረጠ ቃል ላሞካሽህ በሙሉ ሀይሌ ላወድስህ ብርቱዎችን ልታሳፍር ደካማዋን መርጠሃል ብርሃንን እንዳይ ጨለማዬ ላይ በርተሃል እንዴት ነው! የወደድከኝ ፍቅርህ ይገርማል ለኔ ለታናሿ ልጅህን ገልጠህልኛል እንዴት ነው! የወደድከኝ ፍቅርህ ይገርማል የጥበብን ጥጉ ኢየሱስን ገልጠህልኛል