ማልቀስ የለ ወይ ማዘን መተከዝ የለ መቆዘም ርሀብ የለ እርዛት ጥማት የለ ባዶነት ጭንቀት የለ ተስፋመቁረጥ ጦርነት የለ መበጣበጥ በሽታ የለ ጤና ማጣት ወይኔ እያሉ ደግሞ መስጋት የሚበሰብሰውን ስጋ ጥዬ የማይበሰብሰውን ደግሞ ለብሼ ህያውን ጌታ በህያውነት ላመልከው ከመላዕክት ጋር በአንድነት ከቅዱሳንእሄዳለው ናፍቃለው ኦ! ያ ቀን ምን አይነት ክቡር ቀን ነው? አምላኬን ፊት ለፊት የማይበት ለውዴ ምቀኝበት ሁሌ ማመልክበት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል የማዜምበት አንዴ ጎንበስ ብዬ ቀና ባልኩኝ ቁጥር ሊሆንልኝ ላይ የማልጠግበውን ክብር ናፍቃለው የአባቴን አይን በአይኔ ላየው ናፍቆቴን ፍቅሬን ልገናኘው በመላዕክት አጀብ ሊወስደኝ ይመጣልና በክብር እሱ ባለበት በዚያ ለዘላለም ለመኖር ናፍቃለው