Song Lyrics

ገና ገና

Rahel Wendwesen
Kene Ayidelem
ገና ገና ገና ገና ብዙ አያለው ገና እወርሳለው ገና ገና ገና ገና በጥቂቱ ተደንቄ እጄን አጣጥፌ አልቀመጥም የጌታ ስራ እጅግ ብዙ ነው እሮጣለው የኋላዬን እየረሳው ወደ ፊት እዘረጋለው ገና ምንም እንዳልያዝኩኝ እቆጥራለው እሱ ጋ የላቀ አለና እሱ ጋ ገና ገና ኢየሱስ ጋ የሚበልጥ አለና ኢየሱስ ጋ ገና ገና ከውቂያኖስ ላይ በማንኪያ እንዲጨለፍ እንዲሁ የተገለጠው ክብር በህይወቴ ከብዙ ጥቂቱ ቢቀዳ ቢቀዳ ቢቀዳ የማይነጥፍ ምንጭ አለው እግዚአብሔር በኔ የጀመረው ስራ እጅጉን ገና ነው አያዘግየኝ እፈጥናለው ዙሪያዬን ያጀበኝ የተያዝኩበትን ያን እይዛለው ይሄ ነው ሚበጀኝ ይሄ ነው ሚበጀኝ ይሄ ነው ሚረባኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection