ባንተ ደስ ይለኛል ሀሴት አደርጋለው ቢከፋም ቢለማም ደስታዬ ዘላቂ ነው ጌታ ሁሌ ሳስብህ ልቤ ባንተ ያርፋል ማንነትህ ውዴ መልስ ይሆነኛል ጌታ በኔ ሁኔታ አትገመትም ለምን እንዲህ አረክ ከቶ አትባልም ጊዜን አላጠፋ ተጨንቄ ምን ላልጨምር ሁሉን ላንተ ልተው ልጣል ይቅርብኝ ማማረር ጊዜን አላጠፋ ተጨንቄ ምን ላልጨምር ይልቅ በምትኩ አንተን በምስጋና ላክብር ትቼ ጥያቄዬን ትቼ የከበደኝን ትቼ ያቃተኝን ትቼ ችግሬን ላንተ ጥዬ ላምልክህ ተፈትቼ ካለሁበት ገደብ ፈጥኜ ወጥቼ ላምልክህ ዘላለሜን ላክብርህ በአምልኮዬ ምስጋናዬ ይረፍልኝ ልብህ ላምልክህ ዘላለሜን ላክብርህ አምልኮዬ ምስጋናዬ ልብህን ያሳርፍ አምልኮዬ ልብህን ያሳርፍ ምስጋናዬ ልብህን ያሳርፍ እልልታዬ ልብህን ያሳርፍ ዝማሬዬ ልብህን ያሳርፍ ስጋዬና አለም በኔ ላይ ቢማከሩ ሰላሜን ሊያደፈርሱ በክፋት ቢያብሩ ግራ አይገባኝም የምሆነው አይጠፋኝም አባ አንተ እያለህ ልቤ አይታወክብኝም ግራ አይገባኝም የምሆነው አይጠፋኝም ኢየሱስ አንተ እያለህ ልቤ አይታወክብኝም ክፍተቴን እያሳየኝ ባዶውን ማድጋዬን በማጉረምረም ሊሞላው የምስጋና አንደበቴን ብዙ ቢጥር ቢፍጨረጨር በረቂቅ ሀሳቡ ጠላቴ እንደሆን አይሳካለት አይሰምርለትም የልቡ በከበደኝ ላይ ቆሜ ውዴን አመልካለው አፌን በምስጋና ስከፍት ያኔ ድልየኔ ነው