Song Lyrics

አቤት!

Rahel Wendwesen
Kene Ayidelem
የእጆችህን ስራ አይቼ ልገልፅህ ቃልን አጥቼ እጆቼን በአፌ ጭኜ በልቤ እየተደነኩ ምህረትህን እና ፍቅርህን እያሰላሰልኩ አቤት! አቤት! እያልኩ በስራህ እጅግ ተደመምኩ አቤት! የፍቅርህ ጥልቀቱ አቤት! የፍቅርህ ርዝመቱ አቤት! የፍቅርህ ስፋቱ ከአእምሮዬ በላይ ሆነብኝ ትልቅነትህን ሳየው ራሴን እንደ ምንም እቆጥራለው ንፅህናህን ሳስተውለው ራሴን እንደጉድፍ እቆጥራለው ትልቅ ሆነህ ሳለህ ታናሿን ባንተ ፊት አቆምካት ከቅዱሳን ጋራ እንድታዜም በደምህ ቀደስካት ከፍጥረት አይነት በኩራት አደረከኝ በእውነትህም ቃል አስበህ ወለድከኝ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመስግኗል ምስጋናህም በሰማዮች ላይ ከፍ ብሏል ቃልንም አጥቼ መጣው ላከብርህ በዜማዬ አቤት! ስራህ ግሩም ነው ልበልህ ውዱ ጌታዬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection