አዝ፦ ተነሥ (4x) የእግዚአብሔር ክንድ እንደ ጥንቱ ተነሥ ኃይልንም ልበስ እንደ ጥንቱ ተነሥ (2x) ሕዝብህ በምድረ ግብፅ ኑሮ ቢመራቸው ከበግ ጥበቃ ላይ ሙሴን የጠራኸው የዘመናት ንጉሥ እግዚአብሔር ሆይ ዘንዶውን የወጋይ አንተ አይደለህም ወይ አዝ፦ ተነሥ (4x) የእግዚአብሔር ክንድ እንደ ጥንቱ ተነሥ ኃይልንም ልበስ እንደ ጥንቱ ተነሥ የሳተም ይመለስ የዛለም ይበርታ የኃጢአት ምርኮኛ ከእስራት ይፈታ ክንድህን ስንጠብቅ በናፍቆት ዝለናል እስኪ አንድ ጊዜ ጐብኘን ተጠምተናል አዝ፦ ተነሥ (4x) የእግዚአብሔር ክንድ እንደ ጥንቱ ተነሥ ኃይልንም ልበስ እንደ ጥንቱ ተነሥ ያለፉት ባሮችህ አስከብረውሃል ኃይልህ ከላይ ሲወርድ ከአንበሳ ገጥመዋል አንካሶች ሮጠዋል ጋኔሎች ወጥተዋል ጊዜ እይለውጥህም እኛም አይተንሃል አዝ፦ ተነሥ (4x) የእግዚአብሔር ክንድ እንደ ጥንቱ ተነሥ ኃይልንም ልበስ እንደ ጥንቱ ተነሥ