Song Lyrics

የኃያላን ሁሉ ኃያል

ሰማይን የሰራ የምድርም ፈጣሪ በዘለዓለም ዙፋን ለዘለዓለም ኗሪ ገናናነትህን ሰማያት ያውቃሉ ምድርና ሞላዋ ይመሰክራሉ አዝ፦ የኃያላን ሁሉ ኃያል ነህ የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ ነህ የጌቶችም ሁሉ ጌታ ነህ ባለ ታላቅ ግርማ ኤልሻዳይ ነህ በነገስህ ጊዜ ክብርህን ስትለብስ ለተጠቃው ህዝብህ ፊትህን ስትመልስ ድንቅ አድራጐትህን በምድር ስታደርግ በጽድቅህ ስትፈርድ አመጻን ስትጠርግ አዝ፦ የኃያላን ሁሉ ኃያል ነህ የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ ነህ የጌቶችም ሁሉ ጌታ ነህ ባለ ታላቅ ግርማ ኤልሻዳይ ነህ ቃልህን ስትሰጥ በሲና ተራራ በልጆችህ ሰፈር በበረሃው ስፍራ በክብር እሳትህ ተራራውን አጤስከው በመረጥካቸው ፊት ክብርህን ገለጽከው አዝ፦ የኃያላን ሁሉ ኃያል ነህ የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ ነህ የጌቶችም ሁሉ ጌታ ነህ ባለ ታላቅ ግርማ ኤልሻዳይ ነህ የተዳፈሩህን የተነሱብህን ልክህን ሳያውቁ የታጠቁብህን እየቀጣሃቸው ተረቶች ሆነዋል ተፈርተህ ተከብረህ አንተ ግን ኖረሃል አዝ፦ የኃያላን ሁሉ ኃያል ነህ የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ ነህ የጌቶችም ሁሉ ጌታ ነህ ባለ ታላቅ ግርማ ኤልሻዳይ ነህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection