Song Lyrics

መድኃኒታችን

እግዚአብሔር አምላክ እኛን በመውደዱ በዘለዓለም ምክሩ በበጐ ፈቃዱ ውድ ልጁን ልኮ ከኃጥያት አዳነን ገንዘቡም ሊያደርገን ዋጋ ከፍሎ ዋጀን መድኃኒታችን ከአመፅ ተቤዠን በደሙ አንጽቶ ለእራሱ ቀደሰን የመንግሥቱም ወራሽ ወገን አደረገን የናዝሬቱ ኢየሱስ በፀጋ ተሞልቶ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ተቀብቶ ሕዝቡን እየፈታ ዞሮ እየፈወሰ የዲያቢሎስንም ሥራ እያፈረሰ የአምላካችን ማዳን የታዳጊነቱ ዝናውም ሲነገር የኃያልነቱ ጠላት . (1) . ሕግ ደግጋቱን ሊቀ ካህናቱ የአይሁድም አለቆች ሄሮድስ ጲላጦስ የዛ ዘመን ዳኞች ቢመረምሩትም በደል አጡበት ጻድቅ ነው ጌታችን የለውም ስህተት ነውርና እድፍ ነቀፋ የሌለው መዋዕት በመሆን ስለ እኛ የሞተው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ነው ጀርባውን በጅራፍ በእጅጉ ገርፈው እጆቹን እግሮቹን በምስማር ቸንክረው በመስቀል አዋሉት እንደ በደለኛ የነፍሳቸውን ዋስ ያን ታማኝ እረኛ የሚያደርጉትን ባለማወቃቸው አብ ኃጥያታቸውን እንዳይዝባቸው እርሱ ግን ማለደ ይቅር እንዲላቸው መተላለፋችን ተግሳጽ ውጣታችን ደዌ ህመማችን ስቃይ መከራችን በምህረቱ አዋጅ . (2) . ከእዳችን በኢየሱስ ቤዛነት ተሻረ ሞታችን በእርሱ ስላገኘን ሰላምና እርካታ ሃዘንን በደስታ ዋይታን በዕልልታ ስለ ለወጠልን ይክበር የእኛ ጌታ በአንተ ስላገኘን ሰላምና እርካታ ሃዘንን በደስታ ዋይታን በዕልልታ ስለ ለወጥክልን ይክበር የእኛ ጌታ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection