Song Lyrics

ሥራህ ያመሰግንሃል

ሥራህ ያመሰግንሃል ቅዱሳን ያከብሩሃል ፊትነትህ ገብቷቸው ተንበርክኳል ጉልበታቸው አዝ፦ ሃሌሉያ ተመስገን ጌታ ተመስገን ተመስገን (3x) ኢየሱስ ተመስገን እውነትህን ጠብቀሃል ለተበደሉት ፈርደሃል የተጠቃውን ታድገሃል በማዳንህ ከፍ ብለሃል አዝ፦ ሃሌሉያ ተመስገን ጌታ ተመስገን ተመስገን (3x) ኢየሱስ ተመስገን ደሃ አደጉን ተቀብለህ ለተራበ ምግብን ሰጥተህ ምጻተኛ አስጠግተሃል ግዞተኛውን ፈተሃል አዝ፦ ሃሌሉያ ተመስገን ጌታ ተመስገን ተመስገን (3x) ኢየሱስ ተመስገን የተቀደሰ ሥምህን በዜማ ቅኔ ላመስግን በአንተ ሆኖልኝ የመዳን ቀን ስለወጣሁ ከሰቀቀን አዝ፦ ሃሌሉያ ተመስገን ጌታ ተመስገን ተመስገን (3x) ኢየሱስ ተመስገን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection