የጽድቅ ሥራህን ጌታ ሰራህና በጨለማ ላሉ ፀሐይ ወጣችና ከዘለዓለም ጥፋት አንተ ያዳንካቸው በታዳጊነትህ እጅግ ደስ አላቸው (2x) አዝ፦ ሁሉን የምትገዛ ያለህ የነበርህ ትልቁን ኃይልህን ለብሰህ የከበርህ ሥምህ ለዘለዓለም ይመስገን ይባረክ ጉልበት ሁሉ ለአንተ ጌታ ሆይ ይንበርከክ የመስቀል ፍቅርህን ለሰው ይነግራሉ የቅድስናህን ክብር ያወራሉ በክንፎችህ ጥላ ታምነው ይኖራሉ የማዳን ክንድህን ሁልጊዜ ያያሉ (2x) አዝ፦ ሁሉን የምትገዛ ያለህ የነበርህ ትልቁን ኃይልህን ለብሰህ የከበርህ ሥምህ ለዘለዓለም ይመስገን ይባረክ ጉልበት ሁሉ ለአንተ ጌታ ሆይ ይንበርከክ ከሥም ሁሉ በላይ ሥምህ የከበረ ከሰው ልጆች ይልቅ ውበትህ ያማረ የሚመስልህ የለም እጅግ ልዩ ነህ ከፍ ብለህ ንገሥ ግርማ ተሞልተህ (2x) አዝ፦ ሁሉን የምትገዛ ያለህ የነበርህ ትልቁን ኃይልህን ለብሰህ የከበርህ ሥምህ ለዘለዓለም ይመስገን ይባረክ ጉልበት ሁሉ ለአንተ ጌታ ሆይ ይንበርከክ ክብርህ በምድር ሁሉ ይታይ አምላካችን ምላስም ይመስክር ታላቅነትህን በሰማይ በምድር ትሰለጥናለህ ሁሉም ከእግርህ በታች አንተ ትገዛለህ (2x) አዝ፦ ሁሉን የምትገዛ ያለህ የነበርህ ትልቁን ኃይልህን ለብሰህ የከበርህ ሥምህ ለዘለዓለም ይመስገን ይባረክ ጉልበት ሁሉ ለአንተ ጌታ ሆይ ይንበርከክ (3x)