ለህዝቡ ሁሉ የሚሆን የምሥራች ተነገረ ታላቅ ደስታ ነው ልደቱ ይዘምር እስኪ ፍጥረቱ አዝ፦ መጣልን (መጣልን) ጌታ ሊጐበኘን (ሊጐበኘን) ቤዛ ሊሆንልን ከኃጢያት እኛኑ ሊያድን ቃል ሥጋ ሆነና ከድንግል ተወለደልን ህጻን ተወለደ ለእኛ በቤተልሔም በረት ተኛ ለኃጥያተኞች መዳኛ ሊሆን የበጐች እረኛ አዝ፦ መጣልን (መጣልን) ጌታ ሊጐበኘን (ሊጐበኘን) ቤዛ ሊሆንልን ከኃጢያት እኛኑ ሊያድን ቃል ሥጋ ሆነና ከድንግል ተወለደልን ሥሙ የተመሰገነ ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተገልጧልና ልዑሉ ስገዱለት ዕልል በሉ አዝ፦ መጣልን (መጣልን) ጌታ ሊጐበኘን (ሊጐበኘን) ቤዛ ሊሆንልን ከኃጢያት እኛኑ ሊያድን ቃል ሥጋ ሆነና ከድንግል ተወለደልን ተሽቀዳደሙ ኑ እዩት የሚመስልህ የለም በሉት አድንቁት እጅግ አክብሩት ይገባዋል አመስግኑት አዝ፦ መጣልን (መጣልን) ጌታ ሊጐበኘን (ሊጐበኘን) ቤዛ ሊሆንልን ከኃጢያት እኛኑ ሊያድን ቃል ሥጋ ሆነና ከድንግል ተወለደልን በላይ ለእግዚአብሔር ክብር ለእኛም ሰላም በምድር ይሁን ብለን እንዘምር እረፍት አለ መስቀሉ ስር አዝ፦ መጣልን (መጣልን) ጌታ ሊጐበኘን (ሊጐበኘን) ቤዛ ሊሆንልን ከኃጢያት እኛኑ ሊያድን ቃል ሥጋ ሆነና ከድንግል ተወለደልን