Song Lyrics

በክርስቶስ ኢየሱስ

Pastor Tesfaye Gabisso
Yenazretu Yesus
የእግዚአብሔር ፈቃድ ለልጆቹ ይህ ነው መንገዱ ለምርጦቹ ብድራታቸውን ያስተዋሉ የጌታን መስቀል ይመርጣሉ አዝ፦ በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ስለ ሥሙ ይሰደዳሉ እንደ ወርቅም ይፈተናሉ በመጨረሻም ሁሉንም አልፈው የዘለዓለምን ሕይወት ይወርሳሉ ለዚች ዓለም የሚመቹ ነውረኛውን ትርፍ ያከማቹ በኩርነታቸውን አቃለዋል በሥጋ ምቾት ተጠምደዋል አዝ፦ በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ስለ ሥሙ ይሰደዳሉ እንደ ወርቅም ይፈተናሉ በመጨረሻም ሁሉንም አልፈው የዘለዓለምን ሕይወት ይወርሳሉ ጌታን አክብሮ መጐስቆሉ እንደ ጉድፍ የትም መጣሉ የመዳን ምልክት ክብራችን ድል መምቻችን ነው መስቀላችን አዝ፦ በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ስለ ሥሙ ይሰደዳሉ እንደ ወርቅም ይፈተናሉ በመጨረሻም ሁሉንም አልፈው የዘለዓለምን ሕይወት ይወርሳሉ ጌታን ምሰሉ በኑሮአችሁ ከጠፊ ዓለም ምን አላችሁ ውጡ ተለዩ እባካችሁ ፍፁማን ሁኑ በልባችሁ አዝ፦ በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ስለ ሥሙ ይሰደዳሉ እንደ ወርቅም ይፈተናሉ በመጨረሻም ሁሉንም አልፈው የዘለዓለምን ሕይወት ይወርሳሉ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection