Song Lyrics

እግዚአብሔር ሲረዳ

Pastor Tesfaye Gabisso
Yenazretu Yesus
ሕይወት ጐዳና ተስፋ ቆርጦ ሞትን ለሚጠብቀው እረፍትን ፍለጋ ተቅበዝብዞ ሰላሙ ለራቀው ኢየሱስ ነው መፍትሄው ኢየሱስ ነው ሚያድነው (2x) በራስህ ኃይልና ጉልበት ነፍስህን አታድንም በያዝከው ሃብትና ንብረት እርካታን አታገኝም ይልቅስ ቶሎ ብለኸ ና ትምክትህን ተውና እይሱስ ጌታዬ ብለህ ተወለድ እንደገና ያኔ ነው እርካታህ ያኔ ነው ፍፁም ደስታህ (2x) በሕይወት ጐዳና ተስፋ ቆርጦ ሞትን ለሚጠብቀው እረፍትን ፍለጋ ተቅበዝብዞ ሰላሙ ለራቀው ኢየሱስ ነው መፍትሄው ኢየሱስ ነው ሚያድነው (2x) በመስቀል ላይ ጌታ ሲሞት እዳህን ተሸክሞ ከኃጢአት ደዌ ሊያድንህ ስለአንተ እርሱ ቆስሎ ኃጢአትህን ደምስሶልሃል ንጹህ ደሙን አፍስሶ ና ልጄ ናና ይልሃል ስራህንም ጨርሶ ድምጹን ስማ ወዳጄ ተከፍቷል የምህረት ደጄ ድምጹን ስማ ወዳጁእ ተከፍቷል የምህረት ደጄ በሕይወት ጐዳና ተስፋ ቆርጦ ሞትን ለሚጠብቀው እረፍትን ፍለጋ ተቅበዝብዞ ሰላሙ ለራቀው ኢየሱስ ነው መፍትሄው ኢየሱስ ነው ሚያድነው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection