Song Lyrics

ነፍሴ ሆይ

Pastor Tesfaye Gabisso
Yenazretu Yesus
ከጥፋት ጉድጓድ ውስጥ ከረግርግ ጭቃ ያወጣኝ እግሬን በድንጋይ ላይ አቁሞ ያፀናኝ በፀጋው ደግፎ በሕይወት ያኖረኝ ከክፉ ፍላጻ በእጁ የከለለኝ አዝ፦ ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔር አምላክ ነውና ስገጂለት መሀሪው ጌታዬ ምሥጋና ይብዛለት በሕይወቴ ሁሉ እኔም ልገዛለት ቸርነቱን ልንገር ምህረቱን ልዘምር ቅኔን ልቀኝለት ኦ ቅኔን ልቀኝለት ድካምን ህመምን ቁስልን ስብራትን አይቶ ዘመድ ርቆ ሲቆም ኢየሱስ ተጠግቶ በፍቅር አክሞ ሕይወትን ያድሳል ለውለታው ምላሽ ከቶ ምን ይገኛል አዝ፦ ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔር አምላክ ነውና ስገጂለት መሀሪው ጌታዬ ምሥጋና ይብዛለት በሕይወቴ ሁሉ እኔም ልገዛለት ቸርነቱን ልንገር ምህረቱን ልዘምር ቅኔን ልቀኝለት ኦ ቅኔን ልቀኝለት የጫንቃዬን ሸክም ጌታዬ ደርሶ ጣለልኝ የዕዳዬን ጽሕፈት በሞቱ ሻረልኝ ምህረቱ ድንቅ ነው በእኔ ላይ ያሳየው ከእግሩ ሥር ወድቄ ጌታዬን ላክብረው አዝ፦ ነፍሴ ሆይ እግዚአብሔር አምላክ ነውና ስገጂለት መሀሪው ጌታዬ ምሥጋና ይብዛለት በሕይወቴ ሁሉ እኔም ልገዛለት ቸርነቱን ልንገር ምህረቱን ልዘምር ቅኔን ልቀኝለት ኦ ቅኔን ልቀኝለት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection