Song Lyrics

የናዝሬቱ ኢየሱስ

Pastor Tesfaye Gabisso
Yenazretu Yesus
ጊዜው ትዝ ይለናል የተጠራንበት ትዳሩን ሊያሸንፍ ሁሉም በያለበት ሲወጣና ሲወርድ አግኝተህ ስትጠራው አልማረክ ብሎ እምቢ ያለ ማነው አዝ፦ የናዝሬቱ ኢየሱስ ከእኛ ጋራ ያለኸው የሚናወጠውን ወጀብ በሥልጣንህ ያዘዝከው ሥምህ አይጠገብ ደግመን ብንወድሰው ደንቆሮዎች የነበርን መልካም ዜና ሰማን ከብርና ከወርቅ መብለጥህን ተረዳን ሙታን ስታስነሳ እውር ስታበራ ዓይናችን አይቶሃል ድንቅ ሥራ ስትሰራ አዝ፦ የናዝሬቱ ኢየሱስ ከእኛ ጋራ ያለኸው የሚናወጠውን ወጀብ በሥልጣንህ ያዘዝከው ሥምህ አይጠገብ ደግመን ብንወድሰው ከአንተ ጋር ስንጓዝ በዓለም ማዕበል ውስጥ ነፋሱን ገሰጽከው እኛ እንዳንሰምጥ ድምፅህ አይዘነጋም ያ የሚያጽናናው ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ለጠወለገ ሰው አዝ፦ የናዝሬቱ ኢየሱስ ከእኛ ጋራ ያለኸው የሚናወጠውን ወጀብ በሥልጣንህ ያዘዝከው ሥምህ አይጠገብ ደግመን ብንወድሰው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection