Song Lyrics

ስለወደድከኝ ወድሃለው

Pastor Tesfaye Gabisso
Yenazretu Yesus
ለምን ወደድከኝ አልልህም በእርግጥ ወደኸኛል የፍቅርህ መግለጫ ይሄ ነው ለእኔ ተወግተሃል አንተ ለእኔ የሆንከውን ያህል እኔ ለአንተ አልሆንኩም ምን ያህል እንደሆነ አላውቅም ለክቼ አላየሁም አዝ፦ ግን አንድ ነገር አውቃለሁ ስለወደድከኝ ወድሃለሁ (2x) ከእርግማን ስለ ዋጀኸኝ ሞተህ ሸክሜን ስለ ወሰድክ በመንፈስ ቅዱስ ስለ ሞላኸኝ ነፍሴን ስለ ባረክ ፀጋህን አብዝተህ ስለ ሰጠኸኝ ከቶም ስላልተውከኝ ምን ያህል እንደሆነ አላውቅም ለክቼ አላየሁም አዝ፦ ግን አንድ ነገር አውቃለሁ ስለወደድከኝ ወድሃለሁ (2x) ደስ ላሰኝህ እቀናለሁ በሕይወቴ ላከብርህ ሆኖም ከቶ አልጠቀምኩህም ሁሌ ሳሳዝንህ ይልቅ ብዙ አድክሜሃለሁ የትም እየቀረሁ ብዙም ስላላፈራሁ ኢየሱስ ከፍቶኝ አለቅሳለሁ አዝ፦ ግን አንድ ነገር አውቃለሁ ስለወደድከኝ ወድሃለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection