አዝ፦ በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር በከንቱ መታበያችን ይቅር በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር በክርስትናችን ዕድሜ ቆጥረን በልምምዳችን ኮርተን በትህትና መማሩ ቀረና እድገታችን ቆመ ታበየና አዝ፦ በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር በከንቱ መታበያችን ይቅር በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር ባስተያየታችን ጠቢባን ነን ትንኝን እናጠራለን ራሳችንን ማንጻት ሳይቻለን የሌላውን ጉድፍ እናያለን አዝ፦ በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር በከንቱ መታበያችን ይቅር በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር ማደጋችንን እዩልን እያልን በከንቱም እየታበይን አንተንም በዚህ እያሳዘንን ሳይታወቀን ስንቶችን ጐዳን አዝ፦ በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር በከንቱ መታበያችን ይቅር በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር እንደ ሕጻናት የዋሆች አርገን ንጹህ ልብን መልስልን ዓይናችንን እየገለጥህ አንተው አመላልሰን በብርሃንህ አዝ፦ በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር በከንቱ መታበያችን ይቅር በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር በቃል በስርአት ትሁታን ሆነን በፍቅር እየታነፅን በእውነት እንደግ ወደ ኢየሱስ እየታበይን ለምን እንነስ አዝ፦ በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር በከንቱ መታበያችን ይቅር በእውነት አሳድገን ጌታ ሆይ በፍቅር