ከእግርህ ሥር መሆን በብዙ ነገር እንታወካለን ኑሮ ልንገፋ እንጨነቃለን በሥጋ በነፍስ እንባክናለን አርፎ መቀመጥን ከአንተም አፍ መስማትን ገና አሁን ተረዳን ሰምቶ መታዘዝን አዝ፦ ከእግርህ ሥር መሆን ግሩም ነው ቃልህን መማር መልካም ነው የማይጠፋም እድል ነው ጌታ ሆይ (፪x) ሲሰሙህ ደስ እንደሚልህ ጌታችን የአውራ በግ ስብ ብንሰጥህ ከእጃችን ምንም አያረካህ እንደ መስማታችን የእኛ ብቻ ይሰማ እያሉ መለፍለፍ መስማትን ያግዳል ተናግሮ አለማረፍ አዝ፦ ከእግርህ ሥር መሆን ግሩም ነው ቃልህን መማር መልካም ነው የማይጠፋም እድል ነው ጌታ ሆይ (፪x) ደቀ መዝሙርም ሳይሆን ከቶ ሳይማር እራሱን የሚሾም ከሹመቱ ሲሻር ብቻውን ሲወድቅ ያለ አንዳች አጋር ተግሳፅን ያገኛል ጠቢብ አስተውሎ ልማር አስቀድሜ ሩጫ ይቆይ ብሎ አዝ፦ ከእግርህ ሥር መሆን ግሩም ነው ቃልህን መማር መልካም ነው የማይጠፋም እድል ነው ጌታ ሆይ (፪x)