Song Lyrics

መቼ ነው

Pastor Tesfaye Gabisso
Yenazretu Yesus
ማለዳ እየመጣህ ስታነቃኝ ጆሮዬን ከፍተህ ስትናገረኝ በማስተዋል መንገድ ስትመራኝ ከሕይወት ምንጭ ውኃ ስታረካኝ ለምልሞ ነበር ሕይወቴ እንዲህ አልዛለም ጉልበቴ እባክህ አስበኝ አንተ ነህ መድኃኒቴ አዝ፦ መቼ ነው ነቅቼ ድምጽህን የምሰማው ለነፍሴ መጐብኘት መጽናናቴ የሚመጣው (2x) በሌሊት ስነሳ ከእንቅልፌ ሥምህ ነው የሚመጣው ፈጥኖ በአፌ ህመሜን ለአንተ እናገራለሁ ድምጽህን አሰማኝ እማራለሁ ጌታ ሆይ መቃተቴን ስማ ነፍሴ እንደዚህ ተዳክማ እንደ ምን ትዘልቃለች ትካዜን ተሸክማ አዝ፦ መቼ ነው ነቅቼ ድምጽህን የምሰማው ለነፍሴ መጐብኘት መጽናናቴ የሚመጣው (2x) የተወሰነው ስዓትህ ሞልቶ የሀዘኑ ጊዜ አብቅቶ ድካም ድንዛዜ ተወግዶ ኃይልህ የሚሞላኝ ከላይ ወርዶ መቼ ነው ደስ የምሰኘው በጉብኝትህ የምጽናናው ጉልበት ተመልሶ በእግሬ የምቆመው አዝ፦ መቼ ነው ነቅቼ ድምጽህን የምሰማው ለነፍሴ መጐብኘት መጽናናቴ የሚመጣው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection