የአደባባይ ሰው ሆነህ በየማዕዘኑ ላይ ቆመህ ሰውን አይተህ በሰው ታይተህ (2x) በስወር አይቶ በግልጥ የሚከፍልህን በከፍታ ላይ የሚያስኬድህን ረስተህ የለም ወይ አሳዳጊ ጌታህን በስውር የሚቀመጡ ጌታቸውን የሚያደምጡ የሕይወትን ቃል የሚያመጡ (2x) ሰውን ለማነጽ ነቅተው የሚታጠቁ ለበጐ ሥራ ሁሉ የሚበቁ ምስጉኖች ናቸው መማለድን የሚያዉቁ ከእግዚአብሔር የተላከ እርሱ ነው የተባረከ ቃሉን ብቻ እየሰበከ (2x) አንተንስ ማነው አስነስቶ የላከህ በፍጻሜው ላይ ትጠየቃለህ እንደ ሥራህም ያኔ ትከፈላለህ ሥራህ ድካምህ ብዙ ነው አንተነትህን ያጐላው ጌታ እንዳይታይ የጋረደው (2x) እስኪ በእውነት መርምረው ሕይወትህን መፀለይ ትተህ መራቆትህን ኢየሱስን ጋርደህ አንተ መታየትህን ስማው ኢየሱስ ይመክርሃል ተው እረፍ ፀልይ ይልሃል ከእግሮቹ ሥር ሥጋህን ጣል (2x) ያን ጊዜ ጌታ በሰገነት ላይ ወጥቶ ለዓለም ይታያል ብርሃኑ በርቶ ሕይወት ይበዛል የስንዴው ቅንጣት ሞቶ