የሰማይ ብርሃን ጨለማውን ገፍፎ ሲዖል ድል ተነስቶ ሞትም ተሸንፎ በኃጢያት ተወግተው ደክመው ለወደቁ ጥሪው ያስተጋባል ሙታን እንዲነቁ አዝ፦ አንተ የምትተኛ ኢየሱስ ይጠራሃል በሰማዩ ፍቅር ይቀሰቅስሃል ከተሸሸግበት ከሙታን መቃብር ተነሳ ይልሃል ማየት በሌለበት መስማት በጠፋበት ምሬትና ፀፀት ለቅሶ ከሞላበት ምንድን ነው የጣለህ እንደምንስ መጣህ ከሕያዋን ምድር ፈጥነህ ለምን ወጣህ አዝ፦ አንተ የምትተኛ ኢየሱስ ይጠራሃል በሰማዩ ፍቅር ይቀሰቅስሃል ከተሸሸግበት ከሙታን መቃብር ተነሳ ይልሃል ከእንቅልፍ የምትነሳበት ሰዓት ነው ጊዜህን መርምረው ዘመኑን እወቀው እንግዲያውስ ንቃ ተነስ ተመላለስ አንተም ተመልሰህ የጠፉትን መልስ አዝ፦ አንተ የምትተኛ ኢየሱስ ይጠራሃል በሰማዩ ፍቅር ይቀሰቅስሃል ከተሸሸግበት ከሙታን መቃብር ተነሳ ይልሃል ድፍረትህን አትጣል ብድራት አለና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተነስ እንደገና የደከመው እጅህ የዛለው ጉልበትህ ዳግም ተጠናክሮ ያፈራል ሕይወትህ አዝ፦ አንተ የምትተኛ ኢየሱስ ይጠራሃል በሰማዩ ፍቅር ይቀሰቅስሃል ከተሸሸግበት ከሙታን መቃብር ተነሳ ይልሃል